አማርኛ


ውድ የኢንተርነት ድህረ-ገፅ ጎብኞዎች

በዚህ የአማርኛ ዝግጅት ክፍል የተለያዩ የአማርኛ ፅሁፎችን ከእስራኤልና ከዓለም ዙሪያ እያሰባሰብን ለአባቢዎቻችን ለማቅረብ ዝግጅት አለን።

በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጁ ፅሁፎችን ማንበብ የሚችሉት የአማርኛው ፎንት ሲኖርዎት ነው። ለዚህም ቀላል በሆነ መንገድ የአማርኛ ፎንቱን ከዚህ በታች ባለው የኢንተርኔት አድራሻ በማውረድ ወደ ኮምፒውተርዎ (install) በማድረግ የአማርኛውን ፅሁፍ በቀላሉ ማንበብና ከፈለጉም መፃፍ ይችላሉ።

ወገናችንን ከነባሩ ህብረተ-ሰብ ጋር በጥሩ ሁኔታ ተግባብቶ እንዲኖር ይረዳሉ የምትሏቸውን ፅሁፎች ብትልኩልን ለድህረ-ገፁ ተጠቃሚዎች በደስታ ለማቅረብ ዝግጁ ነን።

ፎንቱን ለማውረድ እዚህ በታች ያለውን አድራሻ ይጫኑ

http://mysite.wanadoo-members.co.uk/geez_unicode/Download1.html

ከአዘጋጁ ክፍል

አገር ማለት

አገር በታሪክ በቋንቋ በሀይማኖት በልምድ በተስፋ በደስታና በመክራ ተሳስሮ የሚኖር አንድ ወገን የሆነ ሕዝብ የሚኖርበት የዓለም ክፍል ነው። አገር ማለት አያት ቅድም አያት የተወለዱበት አድገውም በጀግንነት ከውጭ ጠላት እየተከላከሉ ለሕዝብና ለመንግስት የሚጠቅም ሥራ ሠርተው እድሜያቸው ሲደርስም ልጆቻችውን ተክተው የተቀበሩበት ጉድጓድ ነው። በመወለድ እትብት በመሞት አካል ከአፈሩ ጋራ ስለ ሚዋሐዱ የአገሩ አፈር ሕዝብ በላዩ የሚኖርበት ማለት ነው። እግዚአብሔር ከምድርዋ ፍሬ ሕይወት እንዲገኝባት በማድረጉ አገር እያጠባች የምታሳድግ ፍቅርዋ በአጥንት በሥጋ ገብቶ የማይደመሰስ የሆነች እናት ማለት ነው። ከልጅነት ጀምሮ ወንዙን ተራራውን ሜዳውን ቆላውንና ደጋውን በማየት ስለ ማደግ አባቶች በሕህወትና በሞት የሰሩበት ደግ ሥራ በአእምሮ ታትሞ ስለ ቀረ በአገር እስካሉ ሲታይ በስደት ሲሆኑ ሲታሰብ ፍቅርና ናፍቆት የሚያሳድር አገር ነው። አገር አባት እናት ዘመድ ምግብ ጌጥና ሀብት በመሆኑ ድህነትና ጥቃት በመጣ ቁጥር እስካ ሞት ድረስ እንዲሠራበት ከአያት ከቅድመ አያትና ከአባቶች በጥብቅ የተሰጠ የአደራ ገንዘብ ነው።

ከታሪክና ምሳሌ (3 ኛ መጽሐፍ) የተወሰደ



שם:

אימייל:

ההודעה: