ማስታወቂያ
ሰኔ 4 ቀን 2008 ዓ.ም ውድ የቅርያት ኻይም ነዋሪዎች! እንደሚታወቀው ሁሉ በኻይፋ ከተማ ማዘጋጃ ቤትና በቦስቶን ይሁዲዎች ትብበር በከተማዋ ለሚኖሩ ኢትዮጰያውያን ይሁዲዎች በሙሉ በሚቀጥሉት ኮሚቴዎች በትምህርት፣ በጤና፣ በስራ፣ ህብረተሰብንና ቤተሰብን በማጠናከርና በማደራጀት ከነዋሪው ህ/ሰብ ጋር በጥሩ ሁኔታ ተዋህደን ለመኖር እንድንችል የሽሉቪም ፕሮጄክት ተነድፎ ስራውን ከጀመረ እንሆ 2 አመቱን አገባዶ 3 አመቱን ይዟል። ይህ ፕሮጄክት የተገነባው ለ 5 አመት ሲሆን ዋና አላማውም ኢትዮጰያዊው ህ/ሰብ በፕሮጀክቱ ሙሉ ተሳታፊ በመሆን ከላይ በተጠቀሱት ኮሚቴዎች በመግባትና በመሳተፍ ለህብረተሰቡ ይጠቅማሉ፣ ያሻሽላሉ፣ ይረዳሉ ብለን የምናመንባቸውን ፕሮግራሞች በማቅረብና በመወያየት የውሳኔ ተሳታፊዎች እንድንሆን መብቱ ሙሉ በሙሉ ተሰጥቶን ገለፃ ተደርጎ ነበር። ሆኖም ግን ሀብረተሰቡ ሙሉ በሙሉ ይህን የመሰለ የተቀደሰ አላማ ሊጠቀምበት አልቻለም። በሽሉቪም ፕሮግራም በበጎ ፈቃድ ከምንሳተፈው የከተማዋ ነዋሪዎች መካከል ከከተማው ከንቲቫ የህግ ጠበቃ አቶ ዮና ዮሀቭ፣ ወ/ሮ ራኼል መቱኪ የትምህርትና የባህል ክፍል ሀላፊ፣ አቶ ሽሎሞ ቤንኼሞ የቤት ናግለር ሀላፊ፣ ወ/ሮ ሙሉ ብርሐን የሽሉቪም ፕሮግራም ሀላፊ እና ከአቶ ጋቢ ንጉሴ የቅርያት ኻይምና የቅርያት ሽሙኤል ሞቄድ ሽሉቪም ሀላፊ ጋር በ3.6.08 ዓ.ም ተገናኝተን ተወያይተን ነበር። ካቀረብናቸው ሀሳቦች፤ 1. ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ ለደስታም ሆነ ለሀዘን እንግዳ የምንሸኝበት ቦታ (ሞአዶን) ይሰጠን እያልነ መጠየቃችንን አላቋረጥነም። ለዚህ ጉዳይ መፍትሄ እንዲፈለግና መሬት (ክፍት ቦታ) ከፖሊስ ጣቢያው ጀርባ መኖሩን ተናግረናል። 2. ህበረተሰቡ የመረጣቸው የኮሚቴ አባሎችን ስላሉ እነሱን ጠርተው እንዲያነጋግሩ ጥሪ አቅርበናል። 3. የቅርያት ኻይምን ነዋሪ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በተሰበሰበት ተገኝተው ያሉንን ሀሳቦች አንዲያዳምጡንና ለችግሮቻችን መፍትሄ እንዲፈልጉልን ጥሪ አቅርበናል። 4. በክልላችን የተለያዩ ጉዳት የሚያደርሱ እንደ እባብ አይጥና ሌሎችም ተባዮች ለማጥፋት የአካባቢያችን ፅዳት እንዲጠበቅ ጥሪ አቅርበናል። ከላይ ላቀረብናቸው ሀሳቦች የተሰጠን መልስ፤ 1. ከፖሊስ ጣቢያው ጀርባ ያለው መሬት የማን እንደሆነ እንዲያጣራ ለረዳታቸው ትእዛዝ ሰጥተዋል። የማዘጋጃ ቤቱ መሬት ካለ ለህብረተሰቡ ሞአዶን እንዲኖረው ፍላጎታቸው ነው። 2. ኮሚቴውን ጠርተው ለማነጋገር ፈቃደኛ እንደሆኑ ስምምነታቸውን ገልፀዋል። 3. ህብረተሰቡ ተሰባስቦ ከጠራቸው መጥተው እንደሚመጡና የህብረተሰቡን ሀሳብ ለመስማት ደስተኛ መሆናቸውን ገለፀዋል። 4. የአካባቢውን ንፅህና በተመለከተ ለኢሮኒት መ/ቤት በማመልከት መፍትሄ መፈለግ ይቻላል። ውድ ወገኖች ችግሩ የእኛ በኛ አለመግባባታትና አለመነጋገር ነው እንጂ ሃሳባችን የሚሰማና የሚረዳ አናጣም ነበር፣ በመወያየትና በመመካከር መፍትሄ የማይገኝለት ነገር የለም። የወደፊት የእኛና የልጆቻችን ኑሮ ጥሩና የተቃና እንዲሆን የእኛ አንድነትና ትብብር አስፈላጊ መሆኑ ጥርጥር የለውም። ስለዚህ ውድ የቅርያት ኻይም ነዋሪ ኢትዮጵያውያን በሙሉ "ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንደሚባለው ሽማግሌ ወጣት፣ ሴት ወንድ በአንድነት ተሰባስበን በውይይትና በምክክር ለችግሮቻችን መፍትሄ እንድንፈልግ ጥሪያችንን እናቀርባለን። በበጎ ፈቃድ ተሳትፎ የምናደርግ የከተማዋ ነዋሪዎች
መጋቢት 15 ቀን 2008 ዓ.ም በ-31.03.2008 ዓ.ም ከምሽቱ 5 ስዓት በቅርያት ያም ከተማ በአሽኮል ፓይስ አዳራሽ ኢትዮጰያውያን ይሁዲ ሴቶች ወደ እስራኤል አገር ለመምጣት በጉዞ የደረሰባችውን ችግር አስመልክቶ ያሳለፉትን ትዝታ ለማስታወስ ለተሳተፉት ለኮርሱ ተሳታፊዎች ደማቅ የክብር ምሽት ይከበራል። ሚያዝያ 8 ቀን 2008 ዓ.ም የቅርያት ሐይምና የቅርያት ሽሙኤል ነዋሪዎች ሰላም ለእናንተ ይሁን በክልሉ የምንኖር ኢትዮጰያውያን ቤተሰቦች እየሩሳሌምን መጎብኘት። በ-22.4.2008 ዓ.ም ስለሚደረገው ሽርሽር ጉብኝት ስንገልፅላችሁ በደስታ ነው። የቅርያት ሐይምና የቅርያት ሽሙኤል ነዋሪዎች በእየሩሳሌም ቤተሰባዊ ጉብኝት እናደርጋለን። ከቅርያት ሐይምና ከቅርያት ሽሙኤል የምንወጣበት ስዓት ጧት 7.00 ስዓት የምንመለስበት ስዓት19.00 ስዓት ነው። በኮቴሉ፡ በሩቫ ይሁዲ (በይሁዲዎች መኖረያ) እና በሌሎች ቦታዎች ጉብኝት እናደርጋለን። ወላጅ ከልጆች ጋር 20 ሼቄል፡ ባልና ሚስት ልጅ የሌለው 10 ሼቄል ይከፍላል። ለሽርሽሩ ቀን በቂ የሆነ ምግብና ውሀ እነዲሁም ቆብና ሌሎች ለሽርሽር አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን በሙሉ አሟልታችሁ እንድትይዙ በጥብቅ እናሳስባለን።
የሽሉቪም ፕሮግራም የቤተሰብና ህብረተ-ሰብ እና ጤና ኮሚቴ እድሜው ከ-18 አመት በታች ያለ ልጅ ወላጁ አብሮ ካልመጣ ብቻውን መሄድ አይችልም። ወደ እየሩሳሌም ለጉብኝት መሄድ የሚችሉ የተመዘገቡ ቤተሰቦች ብቻ ናቸው።
ቦታ ሳይሞላ በፍጥነት ተመዝገቡ |